ከራበው ሰው ቢሰርቅ ምኑ ነው ሚያስደንቅ
እንዲያው ካልተባለ ነገር እናዳምቅ
የሚሰጠው ካጣ ትንሽ ፍርፋሪ
ወዲያ ለቆሻሻ ከሚደፋው ቀሪ
እየበሰበሰ ለነገ ሲቀመጥ
ይሄኛው ተርቦ ምጽዋትን ሲጠብቅ
ተርፎ ከሚሻግት ሻግቶ ከሚደፋ
በጎን ከሚያስኬደን ሰርክ እየከረፋ
አንድ ዳቦ ምነው ህይወት ለማቆየት
ሰረቀ አስብሎ ዱላ ሚያስይዝበት
ሌባውስ ነበረ ተርፎት የሚደፋው
ላንዷ ሆዱ ሳስቶ ትርፍ እሚያጋብሰው
በልጓም ለጉሞ ለራሱ እንዲመቸው
ጥሬውን ከብስል ያ የሚያማርጠው
ሌባው ዳኛ ሆኖ
ምስክሩ ደግሞ ተገዝቶ በመኖ
ሁለቱ ተባብረው
በዛ በተራበው
አንድ ዳ ቦ ለራብ ማስታገሻ
በበላ ይሉታል ሌባ ነው ቆሻሻ
ይወረውሩታል ወደሰሩት ዋሻ
ስሙን አስከፍተው እሰከ መጨረሻ
ስትጥለው እያየህ አንተ ስታማርጥ
ከመፍረድህ በፊት እሱን ከመቀጥቀጥ
ቢበላ ምናለ ከትራፊው አንዷን
የምትጨረውን ለማስታገስ ሆዱን
No comments:
Post a Comment