አለማወቅህን ደብቀህ ከምትኖር
እንዳልተረዳህው ሃቁን ብትናገር
ነገ ከሚመጣው አስጠያቂ ነገር
ወይ ልኩን ካለፈ ማትወጣው ችግር
እርስክን ማዳንህ መከለልህ ነበር
ብራናን ብራና ያስባለው እውነቱ
እራሱን መቀየር ነው እንጅ መልፋቱ
ቆዳ አልነበረም ወይ ሲፈጠር ከጥንቱ
ከብራና ተማር
እርሳን መቀየር
ግን እንደባር ማሽላ ውስጥህ አረማሞ
ላይህ ተቀባብቶ ደህና ሁኖ ቀልሞ
አውቅለሁ አውቅለሁ ስትል ስታናፋ
እራስክን ደብቀህ ከላይ ስትደነፋ
ቀን የመጣ እንደሆን ምላሽ ሚያስፈልገው
ያን ጊዜ የት ትሄድ ያንተስ ጉድ ብዙ ነው
ያላወቀ ጋነም መቸ ወረደና
ወይም አለማወቅ መች ሃጥያት ሆነና
እንዲህ ተሽቆጥቁጠህ ደጅ የምትጠና
አዋቂ ለመባል በገና ለገና
እርስክን ደብቀህ ከራስህ
ለመኖር ስታስብ ያነኝውን ቀብረህ
ቢንጨበጨብልህ
እንቢልታ ቢነፋ አንቱ ቢበዛብህ
ያልተደከመለት ያልጣርክለት እውቀት
እንዲያው እንደመና ከሰማይ ለማግኘት
ቢያወጡ ቢያወርዱ በከንቱ ቢያስቡት
ጉምን መሰብሰብ ባቅማዳ ለመክተት
No comments:
Post a Comment